ነሀሴ 8 2012 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ድርጅታችን ፖዘቲቭ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት(ፓድ) ላለፉት ዘጠኝ አመታት በድሬዳዋ እና አከባቢዎ በህፃናትና ሴቶች በዋናነት
በአገር ውስጥ ጉዲፈቻ ህፃናት ማቀላቀል፣ ወላጅ አልባና ጎዳና ላይ የሚኖሩና መጠለያ የሌላቸው በማንሳት በማዕከላት በማስገባት
አገልግሎት መስጣት እንዲሁም የአዕምሮ ጤና ችግር ተጠቂ የሆኑ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን
በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ይህን ስራ እውቅና በመስጠት በዘላቂነት ለማዕከል ግንባታ እና አገልግሎት መስጫ የሚሆን
15,000(አስራ አምስት ሺህ) ሜትር ካሬ የከተማ ቦታ መሬት ከሊዝ ነፃ እንዲሰጠን ወስኗል፡፡
ድርጅታችን ፖዘቲቭ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ለተደረገለት ድጋፍ እጅግ በጣም እያመሰገን እነዚህንድጋፍ የሚሹ ወገኖቻችን
ለዘለቄታዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች አጠናክረን የምንሰራ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡